በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ 12ኛው አመታዊ ሀገር አቀፍ የምርምርና የማህበረሰብ ተሳትፎ አውደጥናት ተጀመሯል፡፡
በአውደጥናቱ በሀገሪቱ ከሚገኙ ከፍተኛ የትምህርትና የምርምር ተቋማት እንዲሁም ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች የተውጣጡ ምሁራን ተሳትፈዋል።
ለሁለት ቀናት የሚቆየውን አውደጥናት የዩኒቨርሲቲው ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ዘውድነህ ቶማስ (ዶ/ር) ያስጀመሩት ሲሆን÷ ተግባራዊ ምርምር እና ፈጠራ ለዘላቂ ልማት የሚኖረውን ጉልህ አስተዋፅዖ በመድረኩ በሚካሄድ ሳይንሳዊ ንግግሮች የሚዳሰስ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ ዓመታዊ ሀገራዊ የምርምርና የማህበረሰብ ተሳትፎ ዓውደ ጥናት መድረክ ማካሄዱን የገለጹት ምክትል ፕሬዝዳንቱ፤ ለሁለት ቀናት የሚቆየው 12ኛው አመታዊ ሀገር አቀፍ የምርምር እና የማህበረሰብ ተሳትፎ አውደጥናት “ተግባራዊ ምርምር ለዘላቂ ልማት እና ፈጠራ” በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄድ መሆኑን አመላክተዋል።
በአውደ ጥናቱ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የፈጠራ ሥራዎችና ግኝቶች ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ የሚያሳድሩ 38 የምርምር ረቂቅ ሀሳቦች እና ፖስተሮች የሚቀርቡ መሆኑንም ዶክተር ዘውድነህ አሳውቀዋል።
ዩኒቨርሲቲው ሳይንሳዊ እውቀትን በመተግበር ለህብረተሰቡ የተሻለ ህይወት እና ደህንነት ግንባታ ጥረት እያደረገ ይገኛል ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንቱ፤ አውደ ጥናቱ ዩኒቨርሲቲው በ2030 በቴክኖሎጂ የሚመራ የግብርና ልህቀት ማዕከል ለመሆን የሰነቀው ራዕይ እውን ለማድረግ ከሚካሄዱ በርካታ ጥረቶች መካከል አንዱ መሆኑን አመላክተዋል።
በመድረኩ የተገኙት የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጉቼ ጉሌ (ዶ/ር) በበኩላቸው፡ ጥራት ያለውን መማር ማስተማር፣ ምርምር እና የማህበረሰብ ተሳትፎ ተግባራት በሚፈለገው መልኩ ማሻሻል ከተቻለ ከጥቂት አመታት በኋላ በቴክኖሎጂ መር ግብርናና ጤና የልዕቀት ማዕከል ለመሆን የተያዘውን ራዕይ ማሳካት ይችላል ብለዋል።
በአውደ ጥናት መድረኩ የሚሳተፉ ሳይንቲስቶች እና የሚመለከታቸው አካላት በተግባራዊ ጥናትና ምርምር ጉዳዮች ላይ የሚያቀርቡት ምክረ ሀሳብ በክልሉ እና በአገሪቱ ዘላቂ ልማት ላይ አዎንታዊ አቅም ይፈጥራል ሲሉም ዶክተር ጉቼ ጠቁመዋል።
የተግባራዊ ጥናት ዋና አላማ ፈጣን እና ተግባራዊ ችግሮችን መፍታት መሆኑን የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፤ ዩንቨርሲቲው ይህን አይነት ሀገር አቀፍ ኮንፈረንስ ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ማዘጋጀቱ በቀጣይ በትብብር ለሚሰሩ ሥራዎች ጉልህ ጠቀሜታ እንደሚኖረው አሳውቀዋል።
በአውደ ጥናታዊ መድረኩ ላይ በኢፌዴሪ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር የሹሩን አለማየሁ ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች የተገኙ ሲሆን፤ የአርማወር ሀንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት (AHRI) ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ግዛው በመድረኩ ቁልፍ ንግግር አድርገዋል።
➭ «ዕውቀትን በተግባር!!»
📷የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት!!
➤ ግንቦት 02/2016 ዓ.ም (ወሶዩ)
◼ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟላ መረጃ ለማግኘት ትክክለኛውን የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ🔻
▪Telegram ➲ https://t.me/WolaitaSUniversity
▪Facebook ➲ https://www.facebook.com/profile.php?id=100063820159424
▪YouTube ➲ https://www.youtube.com/…/UC6VukdZbl5iVgZGXG8BkMdw/videos
በዩኒቨርሲቲው 12ኛው አመታዊ ሀገር አቀፍ የምርምር እና የማህበረሰብ ተሳትፎ አውደጥናት ተጀመረ።
- Home
- በዩኒቨርሲቲው 12ኛው አመታዊ ሀገር አቀፍ የምርምር እና የማህበረሰብ ተሳትፎ አውደጥናት ተጀመረ።