«እውነት እና እውቀት ላይ ቆመን ተቋማችንን እና ሀገራችንን ለማሻገር ተቀናጅትን መስራት ይጠበቅብናል።» ፕ/ር ታከለ ታደሰ አዳፍሬ
«እውነት እና እውቀት ላይ ቆመን ተቋማችንን እና ሀገራችንን ለማሻገር ተቀናጅትን መስራት ይጠበቅብናል።» ፕ/ር ታከለ ታደሰ አዳፍሬ
የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት አባላት ከዳውሮ ታርጫ ካምፓስ መምህራን እና ከካምፓሱ የትምህርት ዘርፍ አመራር አካላት ጋር በተለያዩ አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ውይይት አካሂደዋል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕ/ር ታከለ ታደሰ እንደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ሁለንተናዊና ዘላቂ ለውጥ ለማምጣት ዘርፈ ብዙ ተግባራት በተቀናጀና በተደራጀ አግባብ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ተቋሙን ተወዳዳሪ፣ አረንጓዴ፣ ጽዱ እና ሕብረ-ብሔራዊ በማድረጉ ሂደት በተቀናጀ መልኩ እየተሰራ መቆየቱን ፕሬዝዳንቱ ጠቁመው፤ ዕውቀትን በተግባር በመግለጽ ለዩኒቨርሲቲው ራዕይ እውን መሆን በትብብር መስራት ተገቢ መሆኑንም አመላክተዋል።
ለሠላምዊ መማር ማስተማር፣ ለችግር ፈቺ ጥናትና ምርምር፣ ለአሳታፊ የማህበረሰብ አገልግሎት እንዲሁም ለቴክኖሎጂ ሽግግር ውጤታማነት አዳዲስ የአሰራር ስርዓቶችን በመዘርጋት ለተግባራዊነቱ መትጋት አስፈላጊ እንደሆነ
ፕ/ር ታከለ ጠቁመዋል።
በዓለም አቀፍ ግንኙነት መስክ የተጀመሩ ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን ማጠናከር፣ ለመምህራን ምቹ የሥራ ከባባዊ ሁኔታን መፍጠርና የትምህርት ግብዓቶችን በማሟላት ብቁ እና ተወዳዳሪ ምሩቃንን ማፍራት፣ የሕዝብ ተጠቃሚነትን
ማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ በሁሉም የሥራ ዘርፍ መልካም አስተዳደርን ማስፈን እንዲሁም በሁሉም መስክ የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል ትኩረት ይሰጠዋል ሲሉ ፕሬዝዳንቱ አብራርተዋል።
እውነት እና እውቀት ላይ ቆመን ተቋማችንን እና ሀገራችንን ለማሻገር ተቀናጅትን በትጋት መስራት ይጠበቅብናል ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ በዳውሮ ታርጫ ካምፓስ ለሰላማዊ መማር ማስተማር ሥርዓት መረጋገጥ አስፈላጊውን ድጋፋዊ ክትትል እናደርጋለን ሲሉም አሳውቀዋል።
በምክክር መድረኩ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕ/ር ታከለ ታደሰን ጨምሮ የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብርሃም ቦሻ፣ የቢዝነስና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ተክሌ ሌዛ፣ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤክስክዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ወኪል ወልዴ፣ የዳውሮ ታርጫ ካምፓስ ዲን ተባባሪ ፕ/ር መብራቱ ለገሰ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።
በካምፓሱ ከመምህራን እና ከዘርፉ አመራር አካላት ጋር በተደረገው ውይይታ ለዘላቂና ሁለንተናዊ ለውጥ ፋይዳ ያላቸው እንዲሁም ከመልካም አስተዳደር ጋር በተያያዘ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች የማኔጅመንት አባላት ተገቢውን ምላሽ የሰጡ ሲሆን፤ ገንቢ አስተያየቶችን እና አስተዳደራዊ ጥያቄዎችን የተቋም ዕቅድ አካል በማድረግ ፈጣን ምላሽ እንደሚሰጥ አሳውቀዋል።
በካምፓሱ ተጀምረው የቆሙ ቀሪ የግንባታ ፕሮጀክት ሥራዎች እና የመሠረተ ልማት አውታሮች ዝርጋታ ደረጃ በደረጃ ለማጠናቀቅ ተገቢው ትኩረት ተሰጥቶት በተቀናጀ አግባብ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቁርጠኝነት እንደሚሰራ፤ ለመምህራን ምቹ የሥራ ከባቢያዊ ሁኔታን በመፍጠር ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ አዎንታዊ ምላሽ እንደሚሰጥ እንዲሁም ለትምህርት አጋዥ የሆኑ ግብዓቶች በፍጥነት እንደሚሟላ በመድረኩ አቅጣጫ ተቀምጧል።
➭ «ዕውቀትን በተግባር!!»
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት!!
➤ ጥር 07/2015 ዓ.ም
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት
ዌብሳይት፡ http://www.wsu.edu.et/
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን