Visit wolaita Sodo University!!
Visit wolaita Sodo University!!
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲን ይጎብኙ!!
በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጋንደባ ካምፓስ የሚገኘውን «የወላይታ ባሕል ሙዚየም» ይጎብኙ!!
❁✿❁❁✿❁❁✿❁❁✿❁❁✿❁❁✿❁❁✿❁❁✿❁❁✿❁❁✿❁✿❁❁✿❁
በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ (ጋንደባ ካምፓስ) ስለሚገኘው ሙዚየም እውነታዎች
➧ «ቅርስ ያለው ታሪክ አለው» በሚል መርህ በ2012 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ተመሠረተ።
➧ በዩኒቨርሲቲው ዋናው ግቢ–ገንዳባ ካምፓስ የሚገኝ ሲሆን፤ በሀገር በቀል ዕውቀት ተቋም ዳይሬክቶሬት ይተዳደራል።
➧ ውጫዊ እና ውስጣዊ አወቃቀሩ በወላይታ ብሔር ባህላዊ የጎጆ ቤት ቅርጽ የተሰራ ሲሆን፤ የብሔሩን ታሪክና ባህል እንዲገልጽ ተደርጎ የተደራጀ ነው።
➧ ከ300 የሚበልጡ የተለያዩ ባህላዊ እና ታሪካዊ ይዘት ያላቸው ቅርሶችን አደራጅቶ ይዟል።
➧ ቅርሶቹ ለተግባራዊ መማር ማስተማር፥ ለጥናትና ምርምር፣ ለቴክኖሎጂ ሽግግርና ስርጸት፣ ለስልጠና እንዲሁም ቀጣይነት ላለው የቱሪዝም ዕድገት ጉልህ ፋይዳ አላቸው።
➧ የወላይታን ቋንቋ፣ ባህል፣ ታሪክና ቅርስ መጠበቅ፣ ማሳደግና ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ የሙዚየሙ ተቀዳሚ ዓላማ ነው።
➧ በቋንቋው፣ በባህሉ፣ በታሪኩ እና በቅርሱ የሚኮራ እና ማንነቱን የሚገልጽ ትውልድ ለመቅረጽ ሙዚየሙ የላቀ ፋይዳ አለው።
➧ የአካባቢውን ማህበረሰብ ጨምሮ ሙዚየሙን ከ40ሺህ የሚበልጡ የአገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ዜጎች ጎብኝተውታል።
➧ ሙዚየሙ በሚገኝበት ስፍራ የተለያዩ የወላይታ ባህላዊ የቅመማ ቅመም ዝርያዎችን (ናቲራ፣ ጣሎቲያ፣ አጉፒያ፣ ሞርዳሊያ፣ ደቡዋ፣ ከፑዋ፣ ጉጨቻ…) አካቶ ይዟል።
➧ ሙዚየሙን በተለያዩ ቅርሶች የበለጠ ለማበልፀግ ተጨማሪ ባሕላዊ እና ታሪካዊ ቅርሶችን የማሰባሰብና የማደራጀት ተግባር አፅንዖት ተሰጥቶት እየተሰራ ነው።
➧ ሙዚየሙ ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጧቱ 2:00 እስከ ምሽቱ 1:00 ድረስ እንዲሁም ዕለተ እሁድ ከቀኑ 8:00 እስከ 12:00 ለጉብኝት ክፍት ነው።
➧ ይምጡ ይጎብኙ–ብዙ አትርፈው፤ ተደስተው ይመለሳሉ!!
➭ «ዕውቀትን በተግባር!!»
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት!!
➤ ግንቦት 09/2015 ዓ.ም
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት
ፌስቡክWolaita Sodo University4/
ዌብሳይት፡ http://www.wsu.edu.et/
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን