💢በኢትዮጵያ ከሚገኙ አጠቃላይ ዩኒቨርሲቲዎች በምርምር እና በቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች 6ኛ‼


ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ “በምርምርና በቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች” በኢትዮጵያ ከሚገኙ አጠቃላይ ዩኒቨርሲቲዎች ስድስተኛ ደረጃ መያዙ ተገለጸ።
___________________________________
SCIMAGO INSTITUTIONS RANKINGS የተሰኘ የበይነ መረብ ትስስር ገጽ በዓለም፣ በአፍሪካና በኢትዮጵያ የሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን (ዩኒቨርሲቲዎችን) በምርምር፣ በቴክኖሎጂ ፈጠራ ሥራዎችና በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ ያከናወኑት ተግባራት ላይ ትኩረት በማድረግ ተቋማቱን በተለያዩ መስፈርቶች በማወዳደር ደረጃ በመስጠት ይታወቃል።
ድህረ ገጹ እ.አ.አ በግንቦት ወር 2023 ዓ.ም (May 2023) ባወጣው መረጃ በዓለም፥ በአፍሪካ እንዲሁም በኢትዮጵያ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችን በምርምር፣ በፈጠራ ሥራዎች እና በማህበረሰብ አገልግሎት ያከናወኑትን ተግባራት መሰረት በማድረግ የተቋማቱን የደረጃ ሰንጠረዥ ይፋ አድርጓል።
SCIMAGO INSTITUTIONS RANKINGS ድህረ ገጽ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በምርምር እና በቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች በኢትዩጵያ ከሚገኙ አጠቃላይ ዩኒቨርሲቲዎች ስድስተኛ/6ኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አሳውቋል።
በደረጃ ሰንጠረዥ መሰረት “በምርምር መስክ” ጎንደር፣ አዲስ አበባ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ጅማ፣ ሀረማያ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ወሎ፣ አክሱም፣ ባህርዳር፣ መቐሌ፣ አርባ ምንጭ እና ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲዎች በቅደም ተከተል ከ 1-12 ያለውን ደረጃ የያዙ መሆኑን ድህረ ገጹ ጠቁሟል።
እንዲሁም “በፈጠራ ስራዎች” አክሱም፣ ጅማ፣ ሀረማያ፣ አዲስ አበባ፣ ባህር ዳር፣ ወላይታ ሶዶ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ወሎ፣ መቐሌ፣ አርባ ምንጭ፣ ጎንደር እና ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲዎች በቅደም ተከተል ከ 1-12 ያለውን ደረጃ መያዛቸው በድህረ ገጹ ተመላክቷል።
ምርምር ለማካሄድ የሚያስችል ምቹ ከባባዊ ሁኔታን በመፍጠር፣ ተመራማሪዎች የበለጠ እንዲመራመሩ እና የምርምር ውጤታቸውን እንዲያሳትሙ ድጋፍ፣ ክትትል እና አመራር እንዲሁም ማበረታቻ በመስጠት የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ በትብብር መስራት ተገቢ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር አስገንዝቧል።
ዩኒቨርሲቲው በመማር ማስተማር፣ ችግር ፈች ምርምሮችን በመስራት እና የማህበረሰብ አገልግሎት በመስጠት የጀመረውን ስራ አጠናክሮ ሚያስቀጥል መሆኑን እየገለጸ፤ በምርምርና በፈጠራ ሥራዎች ለተገኘው ደረጃ እንኳን
ደስ አለን በማለት መልዕክት አስተላልፏል።
SCIMAGO INSTITUTIONS RANKINGS ድረ ገጽ ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ያገኘውን ደረጃ ለመመልከት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ።
➭ «ዕውቀትን በተግባር!!»

➤ ግንቦት 10/2015 ዓ.ም



አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን



